የDrive አርማ

የDrive ማከማቻ ባህሪያትን ያስሱ

የእርስዎ ነገሮች፣ የእርስዎ መንገድ - Drive ባህሪያት

 

የእርስዎ ማከማቻ ከDrive፣ Gmail እና Google+ ፎቶዎች ጋር አብሮ ይሰራል፣ በዚህም በDrive ላይ ፋይሎችን ማከማቸት፣ የኢሜይል ዓባሪዎችን ማስቀመጥ እና የማንኛቸውም ፎቶዎች ምትኬ ማስቀመጥ ይችላሉ። እንዲሁም ባስፈለገዎት ልክ ተለቅ ያለ የደመና ማከማቻ ዕቅድ መግዛት ይችላሉ።

15 ጊባ ነጻ የGoogle Drive ማከማቻ አርማ

ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ ስላይዶች፣ ፒዲኤፎች – የMicrosoft Office ፋይሎችም ጭምር። ምንም አይነት ፋይል ይሁን ሁሉም ነገር በአስተማ Drive ላይ መቀመጥ ይችላል።

ምስሎችን፣ ሰነዶችን እና ሙዚቃን ጨምሮ የGoogle Drive ፋይል አይነት ዝርዝር

ለማጋራት ካልወሰኑ በቀር ድረስ በDrive ውስጥ ያሉ ፋይሎች የግል ናቸው። ሌሎች ሰዎች የመረጡትን ማንኛውም ፋይል ወይም አቃፊ እንዲመለከቱ፣ አስተያየት እንዲሰጡበት ወይም አርትዖት እንዲያደርጉበት በፍጥነት መጋበዝ ይችላሉ። የመስመር ላይ ትብብር ቀላል ተደርጎ ነው።

የGoogle Drive ግላዊነት እና ማጋሪያ አማራጮች

የእርስዎ ፋይል ደህንነት ወሳኝ ነው። ለዚያ ነው በእርስዎ ዘመናዊ ስልክ፣ ጡባዊ ወይም ኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት ነገር ቢከሰት በDrive ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ፋይል ደህንነት የሚጠበቀው። Drive በGmail እና በሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ላይ ስራ ላይ የሚውለውን ተመሳሳዩ የSSL ደህንነት ፕሮቶኮል በመጠቀም የተመሰጠረ ነው።

የGoogle Drive ደህንነት ቁልፍ

ከGoogle ጋር አብሮ እንዲሰራ የተገነባ

 
የGmail ፎቶ ዓባሪ በአንዲት ጠቅታ በDrive ላይ በመቀመጥ ላይ

በGmail ውስጥ ባለ አንድ አባሪ ላይ ያንዣብቡና የDrive አርማውን ይፈልጉ። እዚህ ላይ ማንኛውም አባሪ በአንዲት ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ለማጋራት በእርስዎ Drive ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ።

የGoogle Drive ፍለጋ ባህሪ ምሳሌ

Drive በምስሎችዎ ውስጥ ያሉ ነገሮችን እና በተቃኙ ሰነዶች ውስጥ ያለ ጽሑፍ ማወቅ ይችላል። በዚህም እንደ «Eiffel Tower» ያለ ቃል መፈለግ እና ያንን ቃል የያዙና እንዲሁም የትክክለኛው አይፈል ታወር ምስሎችን የያዙ የጽሑፍ ሰነዶችን ማግኘት ይችላሉ።

Oregon coast photo stored on Google Drive and shared on Google+

ፎቶዎችዎን በDrive ውስጥ ያስቀምጡትና በGoogle+ ፎቶዎች ነፍስ ሲዘራባቸው ይመልከቱ። ያለጥረት ያ ሙያዊ አርትዖት የተደረገበት መልክ ከእነማዎች፣ ፊልሞች እና ተጨማሪ ነገሮች ጋር ያግኙ።

የGoogle Drive ውሂብ በChromebooks ላይ

Google Drive በChromebooks ውስጥ አብሮገነብ ነው፣ ስለዚህ የእርስዎ ፋይሎች እና ፎቶዎች በራስ-ሰር ምትኬ ይቀመጥላቸዋል። ከአዲሶቹ Chromebooks ጋር 100 ጊባ ነጻ ማከማቻ ለሁለት ዓመት ያገኛሉ።

 

ከመተግበሪያዎች ጋር በበለጠ ብልህነት ይስሩ

 

ይፍጠሩ እና ከሌሎች ጋር ይተባበሩ። በሰነዶችሉሆች እና ስላይዶች መተግበሪያዎቻችን አማካኝነት እየተጓዙ ሳሉ ሰነዶችን እና ፋይሎችን ያጋሩ፣ ተመን ሉሆችን ይገንቡ እና የዝግጅት አቀራረብ ይፍጠሩ።

Google Drive ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች ለማጋራት ይገኛሉ

Google ቅጾች የዳሰሳ ጥናት እንዲያካሂዱ ወይም በአንድ ቀላል የመስመር ላይ ቅጽ አማካኝነት በፍጥነት የቡድን ዝርዝር እንዲፈጥሩ ያስችልዎታል። ከዚያ ውጤቶቹን በጽዳት በተመን ሉህ ውስጥ ተደራጅተው ይመልከቱ።

Google ቅጾች በGoogle Drive ምሳሌ ላይ

Google ስዕሎች አማካኝነት ንድፎችን ያስቀምጡ፣ ወራጅ ገበታዎችን ይፍጠሩ፣ እና ከዚያ በቀላሉ በሌሎች ሰነዶች ላይ ያክሏቸው ወይም በአንድ ድር ጣቢያ ላይ ይክተቷቸው።

የGoogle ስዕሎች አዶ

የመገለጫ ፎቶዎን ያርትዑ፣ የሆነ የመልክ ማሻሻሎችን ያድርጉ፣ የሐሳብ ካርታ ይፍጠሩ እና ተጨማሪ ነገሮችን ያድርጉ። ከ100 በላይ የDrive መተግበሪያዎች በእርስዎ ነገሮች ተጨማሪ እንዲሰሩ ያስችለዎታል። አንዱን በChrome ድር መደብር ውስጥ ካለው የDrive ስብስብ በመጫን ይሞክሯቸው።

ከ100 በላይ የGoogle Drive መተግበሪያዎች ይገኛሉ

Driveን የበለጠ ተጨማሪ ነገሮችን ይስሩበት

 
ፎቶ በAndroid ስልክ በማንሳት ሰነዶችን ወደ Drive የማስቀመጥ ምሳሌ

ሁሉንም የወረቀት ሰነዶችዎን በDrive ለAndroid ይቃኙ። እንደ ደርሰኞች፣ ደብዳቤዎች እና መግለጫዎች ያሉ የሰነዶች ፎቶ ብቻ ያንሱ – እና Drive ወዲያውኑ እንደ ፒዲኤፍ አድርጎ ያስቀምጣቸዋል።

የGoogle Drive መስመር ውጪ ወይም መስመር ላይ ማብሪያ/ማጥፊያ

ለምሳሌ በአውሮፕላን ላይ ሆነው ወይም ጥሩ ግንኙነት በሌለው ህንጻ ውስጥ ሆነው የእርስዎ ስልክ ወይም ጡባዊ አገልግሎት ሲያጣ ፋይሎችን እንዲመለከቷቸው የሚገኙ ያድርጓቸው።

የGoogle Drive ፋይል ክለሳ ታሪክ ምሳሌ

በአብዛኛዎቹ የፋይል አይነቶች ውስጥ እስከ 30 ቀን ወደኋላ ተመልሰው ማየት ይችላሉ፣ ይህ ማን ለውጦችን እንዳደረገ ማየት እና ወደ የድሮ ስሪቶች መመለስ ቀላል ያደርገዋል። ይሄ የፋይል ስሪት መስጠት ቀላል ተደርጎ ነው።