የባህሪያት አጠቃላይ እይታ
Google የግቤት መሣሪያዎች በመረጡት ቋንቋ ይበልጥ በቀለለ ሁኔታ እንዲተይቡ ያስችልዎታል። በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉ የጽሑፍ ግቤት መሣሪያዎች አይነት እናቀርባለን፦
- አይ ኤም ኢ (የግቤት ስልት አርታዒያን) የልወጣ ፕሮግራም በመጠቀም የቁልፍ ጭነቶችዎን ከሌላ ቋንቋ ጋር ያዛምዳቸዋል።
- በቋንቋ ፊደል መጻፍ በአንድ ቋንቋ ጽሑፍ ውስጥ ያሉ ድምጾች/ፎነቲክስ በሌላ ቋንቋ ውስጥ ከድምጾቹ ጋር በተሻለ መልኩ ወደሚዛመድ ጽሑፍ ይቀይራቸዋል። ለምሳሌ፣ በቋንቋ ፊደል መጻፍ «namaste»ን በሂንዲ ወደ «नमस्ते» ይቀይረዋል።
- ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ በእውነተኛ የቁልፍ ሰሌዳዎ ላይ ካሉ ቁልፎች ጋር የሚዛመድ አንድ የቁልፍ ሰሌዳ በማያ ገጽዎ ላይ ያሳያል። በማያ ገጹ ላይ ባለው የቁልፍ ሰሌዳ አቀማመጥ ላይ ተመሥርተው በቀጥታ በሌላ ቋንቋ መተየብ ይችላሉ።
- የእጅ መፃፊያ በጣቶችዎ ቁምፊዎችን በመሳል በጽሑፍ እንዲተይቡ ያስችልዎታል። የእጅ መፃፊያ በአሁኑ ጊዜ በGoogle የግቤት መሣሪያዎች የChrome ቅጥያ ብቻ ነው የሚገኘው።
የግቤት መሣሪያዎችን በGoogle መለያ ቅንብሮች ውስጥ እንዴት ማዋቅወር እንደሚችሉ ይረዱ።
የግቤት መሣሪያዎች በGmail፣ Drive፣ ፍለጋ፣ ትርጉም፣ Chrome እና ChromeOS ጨምሮ በGoogle ምርቶች ውስጥ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ይረዱ።
ይሞክሩት፣ በቀላሉ ወደ የማሳያ ገጻችን ይሂዱ።