Google የግቤት መሣሪያዎች Chrome ስርዓተ ክወና ቅጥያ

Google የግቤት መሳሪያዎች Chrome ስርዓተ ክወና ቅጥያ የሚፈልጉትን ቋንቋ በChrome ስርዓተ ክወና ውስጥ እንዲተይቡ ያስችልዎታል።

በዚህ የChrome ስርዓተ ክወና ቅጥያ እና በGoogle የግቤት መሣሪያዎች Chrome ቅጥያ መካከል ያሉት ዋናዎቹ ልዩነቶች እነዚህ ናቸው፦

ባህሪ የChrome ቅጥያ የChrome ስርዓተ ክወና ቅጥያ
የሚደገፉ የመሣሪያ ስርዓቶች የChrome አሳሽ በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ (Windows፣ Mac፣ Linux) የChrome ስርዓተ ክወና ኮምፒውተሮች ብቻ
ስራዎች በአድራሻ አሞሌው (ኦምኒቦክስ)? አይ አዎ
ከመስመር ውጪ ይሰራል? አይ አዎ

የግቤት መሳሪያዎች ከChromebooks ጋር ተጠቃሏል። በስሪት 28 ወይም ከዚያ በላይ ያለ Chromebook እየተጠቀሙ ከሆነ የግቤት መሳሪያዎችን ለመጠቀም ዝግጁ ነዎት። ያለበለዚያ የእርስዎን Chromebook ያሻሽሉ። Chromium ስርዓተ ክወና እየተጠቀሙ ከሆነ Chrome ስርዓተ ክወና ቅጥያን ከChrome ድር መደብር ይጫኑ።

ወደ ቅንብሮች → የላቁ ቅንብሮችን አሳይ → ቋንቋዎች ይሂዱ። በ«የቋንቋ እና የግቤት ቅንብሮች» አዝራሩ ላይ ጠቅ ያድርጉ። ለመጠቀም የሚፈልጉትን የግቤት መሣሪያ(ዎች) ይምረጡ። [የቋንቋ ስም በራስ ቋንቋ] ([የቋንቋ ስም በChrome የተጠቃሚ ገጽታ ቋንቋ]) የሚል መለያ የተደረገባቸው የግቤት ስልቶች፣ ለምሳሌ፣ हिन्दी (ሂንዲ)፣ በቋንቋ ፊደል መጻፍ አይነት የግቤት መሳሪያዎችን እንደሚያመለክት ያስተውሉ። በቋንቋ ፊደል የመጻፍ መሳሪያዎች የእርስዎን ግብዓት ድምጽን በመከተል ወደ የታለመው ቋንቋው ይለውጡታል።

ከተዋቀረ በኋላ ወደሚፈልጉት የግብዓት ስልት ይለውጡ። አሁን ስራ ላይ በዋለው የግቤት ስልት ላይ ጠቅ ያድርጉ፣ ለምሳሌ፣ በአስጀማሪው ላይ «አሜሪካ» የሚለው ላይ (ማለትም፣ በማያ ገጽዎ ታችኛው ክፍል በስተቀኝ ላይ ያለው የማሳወቂያ አሞሌ/ፓነል)።

የተመረጡ የግቤት ስልቶች ዝርዝር (ከቅጥያው የግቤት ስልቶችን ጨምሮ) ይታያል። ለመጠቀም የሚፈልጉትን የግቤት መሣሪያ ይምረጡ። አዲስ የግቤት መሣሪያ ለማከል «ቋንቋዎችን እና ግቤት አብጅ...»ን ይምረጡ።

አሁን የግቤት መሣሪያ እንደመምረጥዎ መጠን ጠቋሚውን ወደ ማንኛውም የግቤት ሳጥን (ኦምኒቦክስም ይደገፋል) ይውሰዱ፣ አሁን መተየብ መጀመር ይችላሉ።

የግል የግቤት መሣሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ላይ ያሉ ተዛማጅ ጽሑፎች፦