በቋንቋ ፊደል መጻፍ
በቋንቋ ፊደል መጻፊያ ከ20 በላይ ቋንቋዎችን ይደግፋል። በቋንቋ ፊደል መጻፍ ምን እንደሆነና እሱን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለማወቅ የሚከተለውን ቪዲዮ ይመልከቱ። እንዲሁም እስቲ መስመር ላይ ይሞክሩት።
በቋንቋ ፊደል መጻፍ ማለት በፎነቲክ ተመሳሳይነት ላይ በመመስረት አንድ የአጻጻፍ ስርዓት ከሌላ ጋር ማዛመድን ይወክላል። በዚህ መሣሪያ አማካኝነት እርስዎ በላቲን ፊደላት ይተይባሉ (ለምሳሌ፦ a፣ b፣ c ወዘተ.)፣ እነሱ ደግሞ በዒላማው ቋንቋ ውስጥ ተመሳሳይ ድምጽ ወደአላቸው ቁምፊዎች ይቀየራሉ። ለምሳሌ፣ በሂንዲ ቋንቋ ፊደል መጻፊያ ላይ «नमस्ते»ን ለማግኘት «namaste» ብለው መተየብ ይችላሉ፣ «ናማስቴ» የሚል ድምጽ አለው። እርስዎ የሚመርጧቸው የእጩ በቋንቋ ፊደል የተጻፉ ጽሑፎች ዝርዝር ለመጣ ይችላል። «በቋንቋ ፊደል መጻፍ» ከ«ትርጉም» የሚለይ መሆኑን ይልብ ይበሉ፦ ልወጣው የተመሠረተው በትርጉሙ ሳይሆን በድምጽ አወጣጡ ነው።
በቋንቋ ፊደል መጻፊያ ደብዘዝ ያለ የፎነቲክ ማዛመድን ይደግፋል። እርስዎ በቀላሉ የአንድ ቃል ድምጽ አወጣጡ በላቲን ፊደላት ይተይቡና የቋንቋ ፊደል መጻፊያው ይሻላሉ ከተባሉ ግምቶች ጋር ያዛምዳቸዋል። ለምሳሌ፣ ሁለቱም «namaste» እና «nemaste» እጩ ሆነው ወደ «नमस्ते» ይቀየራሉ።

በቋንቋ ፊደል መጻፍን ለመጠቀም፣ የመጀመሪያው እርምጃ የግቤት መሳሪያዎችን ማንቃት ነው። የግቤት መሳሪያዎችን በፍለጋ፣ Gmail፣ Google Drive፣ Youtube፣ ተርጉም፣ Chrome እና Chrome OS ለማንቃት መመሪያዎቹን ይከተሉ።
በቋንቋ ፊደል መጻፍ እንደ
ባለ የቋንቋው አንድ ቁምፊ ይወከላል። የአሁኑን በቋንቋ ፊደል መጻፍ ማብራት/ማጥፋትን ለመለዋወጥ አዶው ላይ ጠቅ ማድረግ ወይም ሌላ
የግብዓት መሳሪያ ለመምረጥ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ቀስት ላይ ጠቅ ማድረግ። በቋንቋ ፊደል መጻፊያ ሲበራ አዝራሩ ደመቅ ያለ ግራጫ
ይሆናል።
በቋንቋ ፊደል መጻፊያ ሲጠቀሙ ቃሉ የሚወክለውን ድምጽ እየፈለጉ በላቲን ቁምፊዎች ይተይቡት። ሲተይቡ ከአጻጻፉ ድምጽ ጋር የሚዛመዱ የእጩ ቃላት ዝርዝር ያያሉ። ከሚከተሉት እርምጃዎች ውስጥ አንዱን በመውሰድ ከዝርዝሩ ውስጥ አንድ ቃል መምረጥ ይችላሉ፦
- የመጀመሪያውን እጩ ለመምረጥ SPACE or ENTERን ይጫኑ።
- አንድ ቃል ላይ ጠቅ ያድርጉ፣
- ከቃሉ ጎን ያለውን ቁጥር ያስገቡ፣
- በአንድ ገጽ ውስጥ ያለውን የእጩዎች ዝርዝር በላይ/ታች ቁልፎች ያስሱት። ገጾችን በPAGEUP/PAGEDOWN ቁልፎች ይግለጡ። የደመቀውን ቃል ለመምረጥ SPACE ወይም ENTERን ይጫኑ።
