የግቤት ስልት (አይ ኤም ኢ)
የግቤት ስልት አርታዒያን (አይ ኤም ኢዎች) የቁልፍ ጭነቶችን በሌላ ቋንቋ ውስጥ ወዳሉ ቁምፊዎች ይቀይሯቸዋል። በርካታ አይ ኤም ኢዎችን እናቀርባለን። ይሞከሯቸው።
አይ ኤም ኢ ለመጠቀም፣ የመጀመሪያው እርምጃ የግቤት መሳሪያዎችን ማንቃት ነው። የግቤት መሳሪያዎችን በፍለጋ፣ Gmail፣ Google Drive፣ Youtube፣ ተርጉም፣ Chrome እና Chrome OS ለማንቃት መመሪያዎቹን ይከተሉ።
አይ ኤም ኢ እንደ
ባለ የቋንቋው አንድ ቁምፊ ይወከላል።የአሁኑን አይ ኤም ኢ ማብራት/ማጥፋትን ለመለዋወጥ አዶው ላይ ጠቅ ማድረግ ወይም ሌላ የግብዓት
መሳሪያ ለመምረጥ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ቀስት ላይ ጠቅ ማድረግ። አይ ኤም ኢ ሲበራ አዝራሩ ደመቅ ያለ ግራጫ
ይሆናል።
የላቲን አይ ኤም ኢዎች
የላቲን አይ ኤም ኢዎች ሰዎች የአሜሪካ ቁልፍ ሰሌዳውን ተጠቅመው የላቲን ጽህፈት ባላቸው ቋንቋዎች እንዲተይቡ ለማገዝ ያነጣጠረ ነው (ለምሳሌ፦ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ኢጣሊያኛ እና ደች)። ባህሪያት ራስ-ሰር የፊደል ምልክቶች፣ ፊደል ማረሚያ እና የቅድመ-ቅጥያ ማጠናቀቅን ያካትታሉ።
የላቲን አይ ኤም ኢዎችን ለመጠቀም፣ የንባብ ምልክት ያልተደረገላቸው ፊደላትን ይተይቡና ትክክለኛው ቃል በአስተያየት ይጠቆማል። ለምሳሌ፣ በፈረንሳይኛ «franca» ብለው ሲተይቡ የቅድመ-ቅጥያ ማጠናቀቅ እጩ ይመለከታሉ።
እጩ «français»ን ለማስገባት TABን ይጫኑ። በዚህ ጊዜ የምንጭ ጽሑፉ «franca»ን ለማስገባት SPACE/ENTERን ይጫኑ።
«francais»ን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ሲተይቡ ስራ ላይ እየዋለ ያለው እጩ ራስ-ንባብ ምልክት እጩ ይሆናል። እጩ «français»ን ለማስገባት SPACE/ENTERን ይጫኑ።
ተጨማሪ እጩዎችን ለማምጣት BACKSPACEን ይጫኑ እና ሁሉንም እጩዎች ያያሉ።
የመጀመሪያው እጩ በጣም የሚተማመነው ራስ-ንባብ ምልክት እጩ ነው፣ እሱም በራስ-ሰር ይደምቃል። ሁለተኛው እጩ የምንጭ ጽሑፉ ነው። ሶስተኛው እና አራተኛው እጩ ዎች የቅድመ-ቅጥያ ማጠናቀቅ እጩዎች ናቸው። 5ኛ እና 6ኛ እጩዎች የፊደል እርማት እጩዎች ናቸው።
ከበርካታ እጩዎች ውስጥ አንድ ቃል ለመምረጥ ከሚከተሉት እርምጃዎች ውስጥ አንዳቸውን ይውሰዱ፦
- የደመቀውን እጩ ለመምረጥ SPACE/ENTERን ይጫኑ፣
- እሱ ላይ ጠቅ ያድርጉ፣
- ከቃሉ ጎን ያለውን ቁጥር ይተይቡ፣
- በአንድ ገጽ ውስጥ ያለውን የእጩዎች ዝርዝር በላይ/ታች ቁልፎች ያስሱት። ገጾችን በወደላይ/ወደታች ቁልፎች ይግለጡ።