ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ

ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ፣ ወይም ደግሞ «የማያ ገጽ ላይ» ቁልፍ ሰሌዳ፣ የትም ይሁኑ ወይም የትኛውም ኮምፒውተር ይጠቀሙ ቀላል በሆነና ወጥነት ባለው መልኩ በቀጥታ በእርስዎ ቋንቋ ፊደል እንዲተይቡ ያስችልዎታል። አንዳንድ የተለመዱ የምናባዊ ቁልፍ ሰሌዳዎች አጠቃቀሞች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ ከ70 በላይ ለሆኑ ቋንቋዎች ያሉ ከ100 የቁልፍ ሰሌዳዎችን ይሸፍናል። እንዴት ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳን መጠቀም እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን የመማሪያ ቪዲዮ ይመልከቱ። እንዲሁም መስመር ላይ ይሞክሩት

ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ ግብዓትን ለመጠቀም፣ የመጀመሪያው እርምጃ የግቤት መሳሪያዎችን ማንቃት ነው። የግቤት መሳሪያዎችን በፍለጋGmailGoogle DriveYoutubeተርጉምChrome እና Chrome OS ለማንቃት መመሪያዎቹን ይከተሉ።

ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳዎች በቁልፍ ሰሌዳ አዶ ነው ይወከላሉ። የአሁኑን አይ ኤም ኢ ማብራት/ማጥፋትን ለመለዋወጥ አዶው ላይ ጠቅ ማድረግ ወይም ሌላ የግብዓት መሳሪያ ለመምረጥ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ቀስት ላይ ጠቅ ማድረግ። አንድ ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ ገባሪ ሲሆን አዝራሩ ደመቅ ያለ ግራጫ ይሆናል።

የእርስዎን ቁልፍ ሰሌዳ እንደ ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳው አድርገው ቆጥረው እሱ ላይ በመተየብ ወይም ደግሞ ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳው ላይ ያሉትን ቁልፎች በቀጥታ በእርስዎ መዳፊት ጠቅ በማድረግ ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳውን ይጠቀሙ።

የማያ ገጽ ላይ ቁልፍ ሰሌዳውን ለማሳነስ የማያ ገጹ ቁልፍ ሰሌዳ ላይኛው ግራ ክፍል ላይ ያለውን ቀስት ጠቅ ያድርጉ።