የእጅ መፃፊያ

የእጅ መጻፊያ ግብዐት ቃላትን በቀጥታ በመዳፊት ወይም በትራክፓድ እንዲጽፉ ያስችልዎታል። የእጅ መጻፊያ ከ50 ቋንቋዎች በላይ ይደግፋል

የእጅ መጻፊያ ግብዓትን ለመጠቀም፣ የመጀመሪያው እርምጃ የግቤት መሳሪያዎችን ማንቃት ነው። የግቤት መሳሪያዎችን በፍለጋGmailGoogle DriveYoutubeተርጉምChrome እና Chrome OS ለማንቃት መመሪያዎቹን ይከተሉ። እባክዎ ከላይ ከተጠቀሱት ምርቶቸ ውስጥ በተወሰኑት ላይ የአንዳንድ ቋንቋዎች የእጅ መጻፊያ ግብዓት ላይገኝ እንደሚችል ያስተውሉ።

የእጅ መጻፊያ ግቤትን በGoogle የግቤት መሳሪያዎች የChrome ቅጥያ ውስጥ እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ ለማወቅ ይህንን የአጋዥ ስልጠና ቪዲዮ ይመልከቱ።

የእጅ መጻፊያ ግብዓት በእርሳስ ይወከላል።የእጅ መጻፊያ ግብዓትን ሲጠቀሙ መዳፊትዎን/ትራክፓድዎን በእጅ ወደመጻፊያ ፓነሉ ያንቀሳቅሱ። ቁምፊዎችን ለመሳል ትራክፓዱን/መዳፊትን እንደተጫኑት ይያዙት። ከእጅ መፃፊያው ጋር የሚመስሉ እጩ ቁምፊዎች ይታያሉ። ቁምፊው ላይ ጠቅ በማድረግ አንድ እጩ ይምረጡ፣ ወይም የመጀመሪያውን እጩ ለመምረጥ የENTER ወይም SPACE ቁልፍን ይጫኑ።